Friday, October 11, 2024
spot_img

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ‹‹መላው ዓለም በምርጫ ቀን ይጋጫሉ ሲለን እኛ ደግሞ እናስተምራቸዋለን›› ሲሉ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 9፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለጂማ ከተማ ነዋሪዎች ባሰሙት ንግግር ‹‹መላው ዓለም በምርጫ ቀን ይጋጫሉ ሲለን እኛ ደግሞ እናስተምራቸዋለን›› ሲሉ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በምርጫው ዕለት መራጮች ድምጽ ከመስጠት ጎን ለጎን ዛፍ በመትከል ለዓለም ትምህርት የሚሆን ተግባር እንዲያከናውኑ ባሳሰቡበት መልዕክታቸው ነው።

‹‹በሚቀጥለው ሰኞ በምናደርገው ምርጫ ‘ዲሞክራሲን እንተክላለን፤ ዛፍም እንተክላለን’ ያልንበት ዋናው ምክንያት መላው ኢትዮጵያ እንደዚህ እንደ ጅማ አረንጓዴ ለብሶ ለአይን የማይጠገብ ውብ እንዲሆን ካለን ፍላጎት ነው›› ያሉት ዐቢይ፤ የጅማ ነዋሪዎችም ሆኑ ኢትዮጵያውያን በዕለቱ ችግኝ እንደሚተክሉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ስቴድየም ለተሰበሰቡ በአስር ሺሕዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻችው ባሰሙት ንግግር፤ ራሳቸው በሚመሩት ብልጽግና ፓርቲም ሆነ በሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ የማያስፈልጉ ያሏቸውን ግለሰቦች ግብር ዘርዝረዋል። ‹‹ከብልጽግናም ሆነ ከሌላ ከህዝባችን የሚሰርቅ ሌባ አያስፈልግንም። ከብልጽግናም ሆነ ሌላ ጠዋታ ማታ ሰርቶ የኢትዮጵያን ብልጽግና እና ልማት የማያረጋግጥ አያስፈልግንም›› ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰኔ 14ቱ ምርጫ ከሚፎካከሩ ኃይሎች መካከል ‹‹ኢትዮጵያን የሚወዱ፣ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚፈልጉ፣ የኢትዮጵያ አንድነትን እና ነጻነትን የሚያከብሩ›› ላሏቸው ተወዳዳሪዎች መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል። ከየትኛውም ፓርቲ ቢሆን፤ ‹‹የኢትዮጵያን ህዝቦች እኩልነት፣ የኢትዮጵያን ህዝቦች አንድነት እንዲሁም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህዝብ ፈርጥ መሆኗን አምኖ›› ለሚሰራ ተወዳዳሪም የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላፈዋል ሲል የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img