Sunday, September 22, 2024
spot_img

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዐረብ ሊግ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 9፣ 2013 ― ዐረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሕዳሴ ግድብን አስመልክተው ያወጡት መግለጫ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዐረብ ሊግ አባል ሀገራት ትላንት በኳታር ዶሃ ባደረጉት ስብሰሳ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ጣልቃ እንዲገባ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ውሳኔን ሙሉ በሙሉ እንደማትቀበል አስታውቋል።
የዐረብ ሊግ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴን በተመለከት የተሳሳተ ውሳኔ ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ያለው ሚኒስቴሩ፤ ይህም ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ላይ ለሚያነሱት መሰረተ ቢስ ጥያቄ ያለውን ድጋፍ ለማመላከት የሚያድርገው መሆኑን ገልጿል።

ሊጉ በግድቡ ዙሪያ ሊጫወት የሚገባውን ገንቢ ሚና ቀድሞ አባክኖታል ያለው ሚኒስቴሩ፤ የግድቡን ጉዳይ ዓለማቀፋዊ ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች የዓባይ ውሃ አጠቃቀም እና ቀጠናዊ ትብብርን ዘላቂ የማያደርጉ ናቸው ብሏል።

የአባይ ውሃን መጠቀም ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ሊረዱት ይገባል ያለው ሚኒስቴሩ፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከድህነት የማውጣት እና ሀይል ፍላጎታቸውን የማሟላት ጉዳይ እንደሆነም አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ህጎች እና መርህዎችን ባከበረ መልኩ የውሃ ሀብቷን እየተጠቀመች ነው ያለው መግለጫው፤ የአባይ ውሃ አጠቃቀም እና የተፋሰሱ ሀገራት ደህንነት ሊጠበቅ የሚችለው በትብብር እና በንግግር ብቻ ነው ብሏል።

የአባይ ወንዝ የተፋሰሱ ሀገራት ጋራ ሀብት እንጂ የግብጽ እና ሱዳን የግል ንብረት አይደልም ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው።

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ስጋቶችን ለመቅረፍ የሚቻላትን ሁሉ ማድረጓንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በህዳሴ ግድበ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች ትርጉም ያለው ስምምነት ላይ እንዳይደርስም ግብጽ እና ሱዳን እንቅፋት ሲሆኑ መቆታቸውን አስታውቋል።

በደቡብ አፍሪካ መሪነት በግድቡ ዙሪያ ሲደረግ በነበረው ድርድር ላይ ሱዳን እና ግብጽ ድርድሩን ለሰባት ጊዜ ማደናቀፋቸውን በማንሳት፤ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሪነት የሚደረገው ድርድርም ውጤት እንዳያመጣ እየሰሩ መሆኑንም አስታውቋል።

ከሰሞኑ የተሰበሰበው የዐረብ ሊግ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በዓባ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደር ጠይቋል፡፡ የዐረብ ሊግ በግድቡ ዙሪያ እየተካሄደ ያለውን ድርድርም አዝጋሚ ነው ሲል ጠርቶታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img