Thursday, October 10, 2024
spot_img

ለዐረብ ኢምሬት መንግሥት ቅርበት ያለው አንድ ሚዲያ ጠ/ሚ ዐቢይን ‹‹አምባገነን›› ሲል ጠራቸው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 8፣ 2013 ― ለተባበሩት ዐረብ ኢምሬት መንግሥት ቅርበት ያለው አንድ ሚዲያ በዘገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ‹‹አምባገነን›› ሲል ጠርቷቸዋል፡፡

ኤሬም ኒውስ የተባለው ይኸው መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ‹‹ሥልጣኑ ከአምላክ እንደተሰጠው የሚያምን›› እና ‹‹በልጅነቱ እናቱ ንጉሥ ትሆናለህ እንዳለችው ደጋግሞ ይናገራል›› ሲል ሰርቶ ባሰራጨው የ5 ደቂቃ የዐረቢኛ ቋንቋ ዘገባው አንስቷል፡፡

አምባገነን ሆነዋል ያላቸውን ጠቅላይ ሚኒስሩን፣ ‹‹በትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ በማካሄዱ ሰበብ›› ጦርነቱ መቀስቀሱን በማስታወስ፣ ‹‹ሰላማዊ ሰው መስሎ መጥቶ አምባገነን የሆነ መሪ ነው›› ሲል ነው የገለጻቸው፡፡

ከጥቅምት ወር አንስቶ በትግራይ እየተካሄደ ባለው ደም አፋሳሽ ጦርነት ተዋጊ ድሮኖችን በማቅረብ ተሳትፋለች ተብሎ በተደጋጋሚ የምትነሳው የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በሀገሪቱ አዲስ አሥተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቅርብ አጋር በመሆን ከፍተኛ የፋይናንስና የልማት ድጋፍ ሲታቀርብ መቆየቷ ይታወቃል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ‹‹የስኬቴ ምንጮች›› የሚሏቸው የቤተ መንግሥትና የፓርኮች ልማት በተባበሩት አረብ ኢምሬት ከፍተኛ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የተሠሩ ስለመሆናቸውም ሲወጡ የቆዩ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገሪቱ ከኢትዮጵያና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ያላትን ግንኙነት በማላላት ላይ እንደምትገኝ ዘገባዎች እያመለከቱ ይገኛሉ። በተለይም በአሜሪካ የዲሞክራቶች አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ፣ አረብ ኢምሬት በአረብ ሰላጤና በአፍሪካ ቀንድ የምታደርጋቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የአሜሪካንን መንግሥት እንዳላስደሰተና ይህም አዲስ የአቋም ለውጥ እንድታደርግ ሳየስገድዳት እንዳልቀረ ነው የሚነገረው፡፡

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በየመንና፣ በሊቢያ የቅጥር ነፍሰ ገዳዮችና ታጣቂዎችን ከላቲን አሜሪካ ሀገራት ጭምር በግዢ በማምጣት በቀጠናው ከፍተኛ አለመረጋጋት ስትፈጥር መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ ቀውስ በጎረቤት ሀገር ሶማሊያም ጭምር እንዲባባስ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ዘገባዎች ያሳያሉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img