Friday, October 11, 2024
spot_img

የአብን ሊቀመንበሩ የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ የዘለቀው ሕወሃት በየትኛውም ሁኔታ መደምሰሰስ ስለነበረበት መሆኑን ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በለጠ ሞላ የጎረቤት አገር ኤርትራ ጠጰር ወደ ኢትዮጵያ የዘለቀው ሕወሃት በየትኛውም ሁኔታ መደምሰስ ስለነበረበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአብን ሊቀመንበሩ ከኢትዮ ትዩብ ጋር ባደረጉት ቆይታ በየትኛውም ሁኔታ ‹‹መደምሰስ›› ነበረበት ያሉት ሕወሃት ሠረዊት መውጋቱን፣ ከተሞችን መደብደቡን አንስተው አገሪቱን ሊበተናት እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያን እንዳልነበረች ላድረግ ገፋ ሲል የነበረው ኃይል መመታት ነበረበት ያያት አቶ በለጠ፣ በየትኛውም ሁኔታ ግን የትግራይ ሕዝብ ዋጋ መክፈል አልነበረበትም ብለዋል፡፡

ሆኖም አቶ በለጠ አሁን የኤርትራ ጦር መውጣት አለበት ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ በቀጥታ ከመመለስ ተቆጥበዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አክለውም የኤርትራ ጦር መውጣት አለበት ነገር ግን ‹‹በሰፊው ልንረዳው ይገባል›› ሲል ተደምጠዋል፡፡

በጥቅምት ወር በፌዴራል መንግስት እና በሕወሃት መካከል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የዘለቁት የኤርትራ ወራደሮች ከቀናት በፊት መውጣት መጀመራቸው ቢነገርም ዝርዝር ጉዳዮች ግን አልወጡም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img