Saturday, November 23, 2024
spot_img

ተዋናይት እፀሕይወት አበበ ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያምን በሥም ማጥፋት ከሰሰች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― በፊልም ትወናዋ የምትታወቀው እፀሕይወት አበበ የትግራይ ቴሌቪዥን የአዲስ አበባ አስተባባሪ ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያምን መክሰሷን አሳውቃለች፡፡

ተዋናይትዋ የቴሌቪዥን ጣቢያውን አስተባባሪ የከሰሰችው ‹‹ምንም ግንኙነት በሌለኝ ጉዳይ ሥሜን ጠቅሶ ባደረሰብኝ የሥም ማጥፋት ነው›› ስትል በማኅራዊ ትስስር ገጽዋ ላይ አስፍራለች፡፡

ለጋዜጠኛው ለክስ መነሻ ሆኗል የተባለው ከቀናት በፊት በአንድ ኦንላይን ሚዲያ ላይ ተዋናይት እፀሕይወት አበበ ባለቤት በሆነችበት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ የምሽት ክበብ ውስጥ አደንዛዥ እጽ እንደሚሸጥበትና የሕወሃት ሰዎች ማምሻ እንደሆነ በአርአያ ተስፋማርያም መነገሩ ነበር፡፡

ተዋናይት እፀሕይወት በሰጠችው ምላሽ በጋዜጠኛው የርሷ ነው በሚል የተጠቀሰው የምሽት ክበብ እርሷ በባለቤትነት የያዘችው እንዳልሆነ ገልጻለች፡፡

እንደ እፀሕይወት ከሆነ ምንም እንኳን ጋዜጠኛው ያቀረበው መረጃ ስህተት መሆኑን ቢያምንም፣ ይቅርታ ለመጠየቅ ፍላጎት እንደሌለው በማሳወቁ ‹‹ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂነት መኖሩን ያውቅ ዘንድ ጉዳዩን በሕግ መያዜ›› ይታወቅ ብላለች፡፡

ጋዜጠኛው ‹‹ከፌዴራል ፖሊስ አገኘሁት ብሎ ያወራው ሕገ ወጥ ምግባርም አብዝቼ የምኮንነውና የምጸየፈው ከሃይማኖቴም፣ ከባህሌም ሆነ አስተዳደግ ስብእናዬ ጋር ሌላው ቢቀር ከእናትነቴ ጋር ፈጽሞ የማይሄድ የምታገለው ነውር ተግባር ነው›› ስትል አስፍራልች፡፡

በተዋናይት እፀሕይወት የተከሰሰው ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም በተለይ ከሕወሃት ከባለሥልጣናት ጋር በተገናኘ ምሥጢር የሚላቸውን መረጃዎች በተለያዩ የኦንላይን እና መደበኛ ሚዲያዎች በመናገር የሚታወቅ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአዲስ አበባ የትግራይ ቴሌቪዥን አስተባባሪ ተደርጎ እንደተሾመ ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img