Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በአምባሳደር ተቀዳ ዓለሙ የሚመራው ልኡክ አሜሪካን ለማግባባት ዛሬ ወደ ዋሺንግተን ይበራል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የጣለውን የቪዛ እገዳ ለማስነሳት የአገሪቱን ባለሥልጣናት እንዲያግባባ የተዋቀረው ልኡክ ዛሬ ምሽቱን ወደ ዋሺንግተን እንደሚያቀና ተሰምቷል፡፡

በዛሬው እለት ወደ አሜሪካ የሚያቀናውና አምባሳደር ተቀዳ ዓለሙን ጨምሮ፣ አምባሳደር ግሩም ዓባይ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታውን ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኢኮኖሚ አማካሪ ማሞ ምኅረቱን የያዘው ቡድን ወደ አገሪቱ ለማቅናት የቪዛ ጣጣውን ባለፈው ሳምንት አጠናቋል ነው የተባለው፡፡

የቀድሞው በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ አምባሳደር ተቀዳ የሚመራው ቡድን በአገሪቱ ቆይታው፣ የቪዛ ማእቀቡን ለማስነሳት ከስቴት ዲፓርትመንት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ከፋይናንስ ተቋማት አለቆች ጋር ተገናኝቶ ይነጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ከጥቂት ሳምንታት በፊት በትግራይ ክልል ካለው ጦርነት ምስቅልቅል ጋር በተገናኘ የፌዴራል መንግስት እና የሕወሃት መሪዎችችን ጨምሮ የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ማእቀብ መጣሉ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img