Sunday, November 24, 2024
spot_img

በኢትዮ ቴሌኮም የ40 በመቶ ድርሻ ተሳተፊ መሆን የሚፈልጉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫቸው ከነገ ጀምሮ ማቅረብ ይችላሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የገንዘብ ሚኒስቴር እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም የቦርድ አማራር በተገኙበት ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር ምዕራፍ መጠናቀቁን አስታወቀዋል፡፡ በዚህም በፈረንጆቹ 2018 የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዞር አንዱ አካል የሆነው የኢትዮ ቴሌኮም የ40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ በሂደቱ ተሳተፊ የሚፈልጉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫ Expression of Interest (EOI) ከነገ ሰኔ፣ 2013 ጀምሮ ማስገባት እንደሚችሉ መንግስት አሳውቋል፡፡

የፍላጎት መግለጫው ማስገቢያው ለአንድ ወር የሚቆይና ዝርዝሩም በገንዘብ ሚኒስቴር እና በመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ እንደሚለቀቅ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዝናቡ ይርጋ ተናገረዋል፡፡

ሂደቱን የዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከግንዘቤ ያስገባ ከመሆኑ ባለፈ በፋይናንስ፣ በንግድ ሥራ ዕቅድ፣ በሕግ እና ታክስ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ በማማከር ረገድ ዴሎይት እንደ ዋና የግብይት አማካሪ ሆኖ የሚሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የመወዳደሪያ ፍላጎት መግለጫውን ተከትሎ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዕቅድ ጥያቄያቸውን የሚያስገቡ ሲሆን፣ ይህም አጠቃላይ ሂደቱ ወቅቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና የተስተካከለ አሰራረርን በመያዝ የሚገለጽ ይሆናል ሲል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img