Monday, September 23, 2024
spot_img

የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ የፊታችን ሰኞ ካልተካሄደ ከምርጫ ራሴን አገልላለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 7፣ 2013 ― የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ ኅብረት ፓርቲ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ ቀደም ብሎ በተያዘለት የዛሬ ሳምንት ሰኔ 14፤ 2013 የማይካሄድ ከሆነ ከስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ራሱን እንደሚያገልል አስታውቋል፡፡

ፓርቲው ይህን ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔን በተመለከተ ዛሬ እሁድ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው።

የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ታደሰ ተፈራ ‹‹ይህ ሪፈረንደም ከምርጫው በላይ ለሕዝቡ ወሳኝ ነው›› ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም በውይይቱ ላይ አንጸባርቀዋል።

ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔው ለመራዘም በምንያትነት ያቀረበው በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ችግር መሆኑን የጠቀሱት አቶ ታደሰ፤ ‹‹የሕዝቡን መሰረታዊ እንቅስቃሴ የገደበ የጸጥታ ችግር የለም›› ሲሉ የቦርዱን ገለጻ የሚቃረን አስተያየት ሰጥተዋል።

‹‹ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መመሪያ አውጥቶ እና ግብረ ኃይል አደራጅቶ ሕዝበ ውሳኔውን አልመራውም›› ሲሉን ቦርዱን የወቀሱት የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባል፤ ተፈጠሩ የተባሉ የጸጥታ ችግሮችም ቢሆን በቦርዱ አማካኝነት በጊዜ ሊፈቱ ይገባ ነበር ሲሉ ተችተዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔን ለማራዘም በቦርዱ የተወሰነውን ውሳኔም በስብሰባው ላይ በግልጽ ተቃውመዋል መባሉን የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img