Friday, October 11, 2024
spot_img

🆕 በኢትዮጵያ የኮሮና ክትባት የወሰዱ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊዮን ተጠጋ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 5፣ 2013 ― በመላ አገሪቱ የኮሮና ክትባት የወሰዱ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊዮን መድረሳቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡ በተያዘው ዓመት መጋቢት ወር መሰጠት የተጀመረው የኮሮና ክትባት እስካሁን ድረስ ለ1 ሚሊዮን 932 ሺሕ 522 ሰዎች ሰዎች ተዳርሷል፡፡

2 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ የአስትራዜኔካ ክትባቶችን በመጀመሪያ ዙር ተረክቦ እንደነበር የገለጸው የጤና ሚኒስቴር፣ በመላ አገሪቱ በቅድሚያ የጤና ባለሞያዎች፣ በእድሜ የገፉና ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እየሰጠ መሆኑን ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ የ4 ሺሕ 235 ሰዎችን ሕይወት የነጠቀ ሲሆን፣ አሁንም 264 ሰዎች በጽኙ ሕሙማን ክፍል ተኝተው ሕክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img