Friday, November 22, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ የሕዝበ ውሳኔ ቀን ለማራዘም ያሳለፈውን ውሣኔ ዳግም እንዲመለከት ተጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 5፣ 2013 ― የደቡብ ምዕራብ ክልል አደራጅ ዓብይ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔ ቀን ለማራዘም ያሳለፈውን ውሣኔ ዳግም እንዲመለከት ጠይቋል።

ኮሚቴው ለህዝበ ውሣኔው ቀደም ብሎ በተያዘለት ጊዜ ከ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ጋር እንዲፈፀም እንዲያደርግም ጠይቋል።

ዓብይ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ የመንግስት ውሣኔና አቅጣጫን ተከትሎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ህዝበ ውሣኔው በተቀመጠለት የጊዜ ሠለዳ እንዲካሄድ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስታውሷል።

ውሳኔውን ተከትሎ ዓብይ ኮሚቴው በአዲስ አበባ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ውሳኔው የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ብሏል። የአካባቢው ህዝቦችም በዘመናት ጥያቄያቸው ላይ ውሳኔ ለማሳረፍ የምርጫውን ቀን እየተጠባበቁ ይገኛልም ነው የተባለው።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ሪፌረንደሙን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለማስፈፀም ላሳየው ተነሳሽነት እና የተግባር እንቅስቃሴ ዓብይ ኮሚቴው ምሥጋናም አቅርቧል። የዳውሮ፣ ካፋ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ ዞኖች እና ኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል እንዲመሰርቱ መወሰኑ ይታወቃል።

‹‹የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ከአጠቃላይ ምርጫው ጋር ሰኔ 14 ቀን ይካሄዳል ተብሎ ታቅዶ የቆየ ቢሆንም ህዝበ ውሳኔው በሚከናውንባቸው ምርጫ ክልሎች በጸጥታ ችግር የተነሳ ድምጽ የማይሰጥባቸው ምርጫ ክልሎች በመኖራቸው የህዝበ ውሳኔውን ምእሉነት ስለሚያጎድለው እና የሁሉንም መራጮች ምርጫ በትክክል መመዘን ስለማይቻል፣ ህዝበ ውሳኔው ከሌሎች የምርጫ ክልሎች ጋር ጷግሜን 1፣ 2013 የሚከናወን ይሆናል።›› ሲል ምርጫ ቦርድ ውሳኔውን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img