Sunday, September 22, 2024
spot_img

የተመድ አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሰብአዊ አቅርቦት እንዳይዳረስ አድርገዋል በሚል አወገዙ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 5፣ 2013 ― የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ላውኮክ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች ሆነ ብለው እርዳታ እንዳይጓጓዝ እየገደቡ ትግራይን በማስራብ ለመደራደሪያነት እየተጠሙ ይገኛሉ በማለት አውግዘዋል፡፡

ማርክ ላውኮክ አሁንም ቢሆን በትግራይ ክልል የሰብአዊ አቅርቦት እየተዳረሰ የሚገኘው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ ብቻ መሆኑን ነው ያመለከቱት፡፡

የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊው የኤርትራ ወታደሮች የእርዳታ እሕል እንዳይጓጓዝ ከልክለዋል ማለታቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመሰቀል ማስተባበላቸውን ሬውተርስ አስነብቧል፡፡

በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት በመንግስትና በተባበሩት መንግስታት የረድኤት ጋሮች ትብብር 3 ነጥብ 3 ሚሊዮኝ ሰዎች እርዳታ እንደቀረበላቸው ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img