Thursday, October 10, 2024
spot_img

በመቐለ ከተማ ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱም ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ አልተገኙም ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 5፣ 2013 ― ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በትግራይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሰበብ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ የመቐለ ከተማ ትምህርት ቤቶች ከሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ግንቦት 30 አንስቶ የተከፈቱ ቢሆንም፣ ተማሪዎች ግን በትምህርር ገበታቸው ላይ እየተገኙ እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮም የተማሪዎቹን በትምህርት ገበታቸው አረጋግጦ፣ ተማሪዎቹ ከቀውስ ስለሆነ የሚመለሱት ቀስ በቀስ ይስተካከላል ብሏል፡፡

የትግራይ ክልለ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዋ አስቴር ይትባረክ በከተማዋ ትምህርት ቤቶቹን ትምህርት ጀምሩ ብለው መመሪያ ቢያስተላልፉም በአንዳንዱ አምስት፣ ሌሎች ጋር ደግሞ ሰባት ተማሪዎችንም ጭምር መምጣታቸውን ገልጸው፣ ሆኖም ከቀውስ ስለተመለሱ ፍርሐትም ስላለ ይህ የሚጠበቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመደበኛ የትምህርት ጊዜያትም ቢሆን በአዲስ የትምህርት ዘመን ላይ ተማሪዎች ቀስ እያሉ ሙሉ ለሙሉ እንደሚመለሱ ያስታወሱት ኃላፊዋ፣ አሁንም ቢሆን ይስተካከላል የሚል እምነት እንዳላቸው ነው ያስረዱት፡፡

የአሜሪካ ድምጽ እንደዘገበው ከሆነ በመቀሌ ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች አሁንም ከክልሉ በጦርነት የተፈናቀሉ ሰዎችን ያስጠለሉ ሲሆን፣ በከተማው የሚታወቀው የዐፄ ዮሐንስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወታደሮች ካምፕ ስለነበር የመዘረፍና የንብርት ውድመት አጋጥሞታል፡፡

የትግራይ ክልል ትምህር ቢሮም አንዳንዶቹ ትምህርት ቤቶች መጠለያ መሆናቸውን አሳውቆ አሁንም ቢሆን አማራጮችን ተጠቅሞ ትምርቱን የማስቀጠል እቅድ መያዙን ነው ያመለከተው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img