Thursday, October 10, 2024
spot_img

አና ጎሜዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላይ ጥያቄ አነሱ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 4፣ 2013 ― በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢ ልዑክ መሪ የነበሩትና የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እንደሚከታተሉ የሚነገርላቸው የፖርቹጋል ዜግነት ያላቸው ወይዘሮ አና ጎሜዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላይ ጥያቄ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስተያየት የሰነዘሩት ወይዘሮ አና ጎሜዝ፣ ከሰሞኑ ካገኟቸው የኦሮሞ ተወላጅ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን አሰቃቂ ታሪኮችን መስማታቸውን እንዲሁም በአገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸው ሕይወት እንደሚያሳስባቸው እንደነገሯቸው አመልክተዋል፡፡

ወይዘሮ አና ከትግራይ ክልል የሚሰሙ የጦር ወንጀሎች እና የረሃብ ዜናን ጨምሮ በመላው አገሪቱ የአፈና እና የግጭት ዜናዎች መበርከታቸውን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህን ሁኔታዎች የዘረዘሩት ወይዘሮ አና ጎሜዝ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቀበሉት ኃላፊነት ከባድ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያውያን አሁን ምን ተስፋ አላቸው ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ሰንዝረዋል፡፡

በቅርብ ጊዜያት በተለይ በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሚወቅሱ የውጭ አካላት መበርከታቸው ይስተዋላል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img