Thursday, October 10, 2024
spot_img

ልማት ባንክ ብድሩን መክፈል ያልቻለውን የቱርክ ኩባንያ አስተዳደር መረከቡ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 4፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ተበድሮ በአግባቡ መክፈል ያልቻለው በቱርካውያን ባለቤትነት የተመሰረተውን ኢቱር ቴክስታይልን ተረክቦ ማስተዳደር መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ልማት ባንክ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካው የተበደረውን ገንዘብ በአግባቡ መመለስ ባለመቻሉ ለብድር አመላለስ በዋስትናነት የተመዘገበውን በአዳማ ከተማ ያለውን የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካውን ነው ተከክቦ ማስተዳደር ጀምሯል፡፡

የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካውን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ግለሰቦችን በማንሳትም ልማት ባንክ ለኩባንያው ሥራ አስኪያጅ፣ የፋይናንስ ኃላፊ፣ የማርኬቲንግ እና ሌሎች ኃላፊዎችን ራሱ መሾሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡

በ1950ዎቹ በቱርክ የተቋቋመውና በጨርቃ ጨርቅ ምርቶች አለም አቀፍ አቅራቢነት የሚታወቀው የዩክሴል ቴክስታይል እህት ኩባንያ የሆነው ኢቱር ቴክስታይል ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ስራ የጀመረው በ2002 ነበር። በወቅቱ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቢሊዮን የሚቆጠር ብድር ከወሰዱ መሰረታቸውን ቱርክ ካደረጉ ፋብሪካዎች ውስጥ የሚመደብ ነው።

አዳማ ላይ ባቋቋመው ፋብሪካ በዋነኝነት ክር የሚያመርት ሲሆን፣ ክርን በመጠቀም የተለያዩ ምርቶችን ለሚያመርቱ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ግብአት ሲያቀርብ የቆየ ነው።

ነገር ግን እንደ ሌሎች የቱርክ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የወሰደውን ብድር በጊዜው መክፈል አልቻለም። ከስድስት ዓመት ወዲህ ፋብሪካው የልማት ባንክን ብድር መመለስ ስላልቻለ የተበላሸ ብድር መዝገብ ውስጥ ገብቶ የቆነ ነው።

በተደጋጋሚ ብድሩን እንዲመልስ ከልማት ባንኩ ደብዳቤ የተጻፈለት ቢሆንም፣ በተገቢው መንገድ ብድሩን እንዳልከፈለ ነው የተነገረው፡፡

በተመሳሳይ አልሲ አዲስና አይካ አዲስ የሚባሉ ሁለት የቱርክ ኩባንያዎች ልክ እንደ ኢቱር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቢሊየን የሚቆጠር ብር ተበድረው መክፈል ስላልቻሉ ባንኩ ገንዘቡን ለማስመለስ ተደጋጋሚ ጨረታ ቢያወጣው፣ የፋብሪካዎቹ ዋጋ ብድሩን የማያስመልስ ብቻም ሳይሆን የወሰዱት ብድርና ያስገቧቸው ማሽኖች ዋጋ ሊመጣጠን ባለመቻሉ ተረክቦ ማስተዳደር ከጀመረ መሰንበቱንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img