Thursday, October 10, 2024
spot_img

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከመተከል ግጭት ጋር በተገናኘ 600 የሚጠጉ ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 4፣ 2013 ― የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሠረት በማድረግ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ግድያ፣ ማፈናቀል እንዲሁም ንብረት ማውደም ውስጥ እጃቸው አለበት ባላቸው 600 የሚጠጉ ግለሰቦች ላይ ክሥ መመሥረቱን አስታውቋል።

ከተከሳሾቹ መካከል በየደረጃው ያሉ የአመራር አባላት እንደሚገኙበት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የተደራጀና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ላፒሶ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተር ጀነራሉ ተከሳሾቹ በቤንሻጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በሚገኙት በድባጤ ወረዳ 296፣ በጉባ ወረዳ 188 እና ቡለን ላይ ደግሞ 141 ግለሰቦች ናቸው፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ወንጀሉን ፈጽመው በመሸሻቸው በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉም ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች በክልሉ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ 210 ሰዎች፣ በጉባ 83 ሰዎች እና በድባጤ ወረዳ የ346 ሰዎች ሕይወት እንዲቀጠፍ ምክንያት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img