Wednesday, December 4, 2024
spot_img

ሶማሊያ ወታደሮቿ በትግራይ ግጭት ተሳትፈዋል መባሉን ውድቅ አደረገች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 4፣ 2013 ― ሶማሊያ ወታደሮቿ በትግራይ ክልል በተካሄደዉ ጦርነቱን ላይ ተሳትፈዋል በሚል የሚወጡ መረጃዎችን በድጋሚ ውድቅ አድርጋለች፡፡

የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት ዑስማን ዱቤ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የሚወጡ መረጃዎችን መሠረተ ቢስ አሉባልታዎች እና ከፖለቲካ የመነጩ ፕሮፖጋንዳዎች ናቸው ብለዋቸዋል፡፡

የሶማሊያ መንግሥት ምላሹን የሰጠው ከሰሞኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰነድ ኤርትራ ለሥልጠና የሄዱ ወታደሮች በትግራይ ክልል ጦርነት መሳተፋቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የወታደሮቹ ቤተሰቦች ለዳግም ተቃውሞ አደባባይ በመውጣታቸው ነው፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በሪፖርቱ ወታደሮቹ በአክሱም ጭፍጨፋ መሳተፋቸውንም ያመለከተ ቢሆንም፣ የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ግን በየትኛውም የትግራይ አካባቢ ወታደሮቻችን አልተሳተፉም፣ አሁንም የሉም ብለዋል፡፡

ዑስማን ዱቤ አክለውም ወታደሮቹ ለምን ኤርትራ እንደሄዱ ባብራሩበት ወቅት የሶማሊያን ጦር ለመገንባትና ለማጠናከር እገዛ አንደሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት ኤርትራም ለወታደሮቻችን ስልጠናዎችን ትሰጥልናለች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img