Thursday, October 10, 2024
spot_img

የተመድ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ኃላፊ በትግራይ ክልል ረሃብ ተከስቷል ሲሉ ተናገሩ

እንዲጠቀሙበት ተጠየቀ አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በትግራይ ክልል ረሃብ ተከስቷል ሲሉ ዛሬ በበይነ መረብ ለተሰበሰቡት የአሜሪካው ዩኤስአይዲ እና የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ እና ልማት ዕርዳታ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተናግረዋል።

በዚሁ ስብሰባ ተወያዮቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታን እንዳያሰናክልና ግጭት እንዲያቆም እና ርሃብ እንዳይከሰት ለማስቀረት ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ጫና እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪም ተወያዮቹ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የኤርትራ ወታደሮች ባስቸኳይ ከክልሉ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል በስብሰባው ላይ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር እንዲሰበሰብ በተመድ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሊንዳ ግሪንፊልድ ዛሬ ጥሪ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ከነገው የቡድን 7 ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ቀድሞ በተደረገው ስብሰባ የትግራይ ክልል ጉዳይ በነገው ላይ አጀንዳ እንደሚሆን በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ጀፍሪ ፊልትማን ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img