እንዲጠቀሙበት ተጠየቀ አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ጅቡቲ ከቀናት በፊት ሦስት ግለሰቦችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ መስጠቷን አውግዟል፡፡
ድርጅቱ የጅቡቲ ባለሥልጣናት ይህን በማድረጋቸው ዓለም አቀፍ ሕግጋትን ጥሰዋል ነው ያለው፡፡
የጅቡቲ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል የተባሉት ሦስቱን ግለሰቦች የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ‹‹አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እና በጥብቅ ሲፈለጉ የነበሩ የአሸባሪው ሕወሃት ቡድን አባላት›› ናቸው ብሎ የነበረ ሲሆን፣ የስደተኞች ድርጅቱ ግን ከሦስቱ ግለሰቦች መካከል ሁለቱ በጅቡቲ ይኖሩ የነበሩ ስደተኞች መሆናቸውን አሳውቋል፡፡
የስደተኞች ኮሚሽኑ ጥገኝነት ጠያቂ ሰዎች ከየትም ይምጡ ከተጠለሉበት አገር ጉዳት ሊደርስባቸው የሚችሉበት ቦታ ሊመለሱ እንደማይገባ በመጥቀስ፣ የጅቡቲ መንግሥት ኃላፊዎች የወሰዱትን እርምጃ ኮንኗል፡፡
‹‹አገሪቱን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እና በጥብቅ ሲፈለጉ ነበሩ›› የተባሉትና በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሃት አባላት እንደሆኑ የተነገረው አቶ ሐብቶም ገብረስላሴ ወልዩ፣ አቶ መሰለ ታመነ እሸቱ እና ኮለኔል መሐመድ በሪሁ ኑር ናቸው፡፡