Monday, November 25, 2024
spot_img

በቅርቡ በደምቢ ዶሎ በአደባባይ የተረሸነው ወጣት ጉዳይ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ለሰው ሕይወት ግድየለሽ መሆናቸውን አመልካች ነው አለ

እንዲጠቀሙበት ተጠየቀ አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― ሂዩማን ራይትስ ዎች በቅርቡ በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የኦነግ ሸኔ አባል ነው በሚል በደምቢዶሎ በአደባባይ የተረሸነው አማኑኤል ሐብታሙ የተባለ ወጣት ጉዳይ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ለሰው ሕይወት ግድየለሽ መሆናቸውን አመልካች መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሂዩማን ራይትስ ዎች የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ላቲሽያ ባደር የጸጥታ አካላትም ወጣቱን በአደባባይ ሲረሸኑ ቀርጸው መልቃቀቸውም ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነው ተግባራቸው የሚያመጣብን ምንም ነገር የለም ብለው እንደሚያስቡ የሚያመለክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ሪፖርት የሚያደርገው ተቋሙ፣ የወጣቱን አማኑኤል ሐብታሙን ግድያ አስመልክቶ አስራ አንድ ሰዎችን ቃለ ምልልስ ማድረጉን እንዲሁም የወጡ የምስል ማሰረጃዎችን እና መንግሥት የሰጠውን ምላሽ በመመልከት አገኘሁት ያለውን ይፋ አድርጓል፡፡

እንደ ሒዩማን ራይትስ ዎች ከሆነ ባለፈው ወር ግንቦት 3፣ 2013 ጧት ላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ወጣቱን በቤቱ አካባቢ በቁጥጥር ስር ባዋሉበት ወቅት ጭንቅላቱን በሰደፍ መቶ ከመጣል አንስቶ የተለያየ ድብደባ እንደፈጸሙበትና ኋላም ወደ ከተማው መሐል በመውሰድ ሰዎችን እንዲሰበሰቡ አድርገው ረሽነውታል ብሏል፡፡

ግድያውን ተከትሎም የወጣቱ እናት እና አባት ልጃችንን እንቅበር አስከሬን ስጡን ብለው ቢጠይቁም ተከልክለው የነበረ ሲሆን፣ አስከሬን የጠየቁት ወላጆቹ በጸጥታ አካላት መዋከብ እና እንግልት፣ ባስ ሲልም በትር ተሰንዝሮባቸዋል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች ጨምሮም ከወጣቱ ግድያ በኋላ በአካባቢው ነዋሪዎች በጸጥታ አካላት ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው የገለጸ ሲሆን፣ በለቀስተኞች ቤት ውስጥ የተገኙት የሟቹን አባት ጨምሮ ሌሎቸ መታሰራቸውን አመልክቷል፡፡

የተቋሙ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ላቲሽያ ባደር የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አሁንም ለሚፈጸሙ ግድያዎችን መርምሮ ፍትህ ከማስፈን ይልቅ ያላቸውን ንቀት ማሳየት ቀጥለዋል ነው ያሉት፡፡

ባለፈው ወር በደምቢዶሎ በጸጥታ ኃይሎች በአደባባይ የተረሸነው አማኑኤል ሐብታሙ የተባለው ወጣት የአስረኛ ክፍል ተማሪ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img