Thursday, October 10, 2024
spot_img

የኢትዮጵያን ቴሌኮም ገበያ የተቀላቀለው ጥምረት 8 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ይዞ እንደሚገባ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― በትላንትናው በኢትዮጵያ መንግሥት እና የቴሌኮም አገልግሎት ለማቅረብ ፍቃድ ባገኘው ጥምረት መካከል የፍቃድ ስምምነት ፊርማ መካሄዱን ተከትሎ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ቤተ መንግሥት በትዊተር ገጹ ላይ ጥምረቱ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 8 ቢሊየን ዶላር የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ይዞ እንደሚገባ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፍ የተቋማት ስብስብ ለሆነው ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ መስጠቷ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለውና የስድስት ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ተቋም የቴሌኮም ፍቃድ በማሸነፍ በዘርፉ ይሰማራል።

ይህን ጥምረት የሚመራው የኬንያው ሳፋሪኮም ሲሆን፤ የዩናይትድ ኪንግደሙ ቮዳፎን እና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም፣ የጃፓኑ ሱሚቶሞ እንዲሁም ዲኤፍሲ በጥምረቱ ተካተዋል።

ቢቢሲ የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ ፒተር አንዴግዋ ጥምረቱ ሥራውን በፈረንጆቹ በ2022 አጋማሽ ላይ እንደሚጀምር ነግረውኛል ብሏል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥምረቱ ጥራቱን የጠበቀ የድምጽ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረብ፤ የኢትዮጵያን ወደ ዲጂታል ሥርዓት የመቀየር ፍላጎትን እውን ማድረግ እና የሰዎችን ሕይወት ማሻሻል ዓላማ እንዳደረገ ተናግረዋል።
የ110 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ በመጀመሪያዎቹ 5 ዓመታት አብዛኛው ሕዝብ ጋር እንደርሳለን ብለው ማቀዳቸውን አክለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img