አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው እያለፈ እንደሚገኝ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊይ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በትግራይ ጉዳይ ጊዜው እያለቀ ነው ያሉ ሲሆን፣ አሁንም ቢሆን በክልሉ ያልተገደበ የሰብአዊ አቅርቦት እንዲዳረስ ሁሉም አካላት ቁረጠኝነት ሊያሳዩ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡
በተመሳሳይ ከሁለት ቀናት በፊት በትግራይ ክልል በርካታ አካባቢዎች በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ዋና ጸሐፊው በክልሉ ‹‹አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው›› ሲሉም ገልጸው ነበር፡፡