Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ጠ/ሚ ዐቢይ ከማእቀቡ ጋር በተገናኘ ለማግባባት በአምባሳደር ተቀዳ ዓለሙ የተመራ ቡድን ወደ አሜሪካ ለመላክ ማቀዳቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ ጋር ያጋጠማቸውን ዲፕሎማሲያዊ ችግር ለመፍታት በአንጋፋው የቀድሞው ዲፕሎማት አምባሳደር ተቀዳ ዓለሙ የተመራ ቡድን ወደ አገሪቱ ለመላክ ማቀዳቸው ተሰምቷል፡፡

ለዚሁ እንዲረዳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድሚያ አምባሳደር ተቀዳን ማናገራቸውን ቲኤፍአይ የተባለ ገጽ አስነብቧል፡፡

አምባሳደር ተቀዳ የሚመሩትና አሜሪካ የጣለችውን እቀባ እንድታነሳ የሚያግባባውን ቡድን አምባሳደር ግሩም ዓባይ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ድኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኢኮኖሚ አማካሪ ማሞ ምህረቱን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ነገሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰቡት መንገድ የሚጓዙ ከሆነ አራቱ ተወካዮች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ ይሆናል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ማእቀብ መጣሉ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ማእቀቡ አሁን ወደ አገሪቱ ሊያቀኑ ነው የተባሉትን አራት ተወካዮች የሚያካትት ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ቡድኑን የሚመሩት አምባሳደር ተቀዳ ዓለሙ ከደርግ መንግሥት ጊዜ ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታን ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት ሲሆን፣ ለረዥም ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ቆይተው በነሐሴ 2010 የተነሱ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img