Tuesday, December 3, 2024
spot_img

የሶማሊያ ወታደሮች በአክሱም ጭፍጨፋ መሳተፋቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― በኤርትራ በሥልጠና ላይ የነበሩ የሶማሊያ ወታደሮች በአክሱም ጭፍጨፋ ላይ ተሳትፎ እንደነበራቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ጋሮው ኦንላይን ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል ጦርነት ተሳፈዋል የተባሉት እነዚህ ወታደሮች ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ባይጠቀስም፣ ከነበሩበት የጦር ካምፕ ከኤርትራ ወታደሮች ጋር ባንድነት ወደ ትግራይ ዘልቀዋል ነው የተባለው፡፡

የሶማሊያ ወታደሮች ተሳትፎ አላቸው ከተባለበት የአክሱም ጭፍጨፋ በተጨማሪ በትግራይ ክልል መቀመጫ መቀሌ ከተማ መታየታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

አሁን በትግራይ ጦርነት ላይ መሳተፋቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተረጋግጧል የተባሉትን የሶማሊያ ወታደሮችን በሚመለከት የፌዴራል መንግስቱ እና የሕወሃት ኃይሎች ጦርነት በጀመረ ከጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይኸው የዜና ተቋም በጦርነቱ ዘምተዋል የሚል መረጃ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ግን አስተባብለው ነበር፡፡

ወታደሮቹ ለሥልጠና ሄደው ተሰውረዋል ያሉ የወታደሮቹ ቤተሰቦችም በዚያኑ ሰሞን ልጆቻችንን መልሱልን ሲሉ በሞቃዲሾ አደባባዮች በሰልፍ ጭምር ጠይቀው ነበር፡፡

ወታደሮቹ በትግራይ ጦርነት ተሳትፎ አላቸው መባሉን በተመለከተ አሁንም ከወታደሮቹ ባለቤት የሶማሊያ፣ ሲሰለጥኑባት ነበር የተባለችው የኤርትራም ሆነ ወታደሮቹን ተጠቅሟል የተባለው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img