Sunday, October 6, 2024
spot_img

‹ሔመቲ› የሚመሩትን የሚሊሺያ ጦር ይዘው የሱዳን መከላከያ ኃይልን መቀላቀል እንደማይፈልጉ መናገራቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 1፣ 2013 ― የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ሌተናል ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ ወይም ሔመቲ የሚመሩትን የሚሊሺያ ጦር ይዘው የሱዳን መከላከያ ኃይልን መቀላቀል እንደማይፈልጉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

ከፍተኛ ኃይል ያላቸው ግለሰብ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ምክትል ኃላፊው ሌተናል ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ የአገሪቱን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል የተባለውን ጦርም የሚመሩ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በሕዳሴ ግድብ ዙርያ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ካለ ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የዛሬ ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ተገኝተው የነበሩት ሌተናል ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ፣ በቅርቡ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የገቡበትን የድንበር ውጥረት በተመለከተም ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግሮ ነበር፡፡

ዳግሎ በአገራቱ መካከል ለተገባው ውጥረት የመጀመሪያውም ሆነ የመጨረሻው መፍትሔ መደራደር ነው የሚል አቋም አንጸባርቀዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img