Thursday, October 10, 2024
spot_img

ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አየሠራሁ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 30፣ 2013 ― በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ስደተኞቹ የመጡበት አካባቢ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነ በመሆኑ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እያመቻቸሁ ነው ብሏል፡፡

ኤምባሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው፣ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ስደተኞች ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለመመለስ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጧል፡፡

በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት ሰበብ በርካቶች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የሚታወስ ነው፡፡ እንደ ዩኒሴፍ ከሆነ የተሰደዱት ሰዎች ከ60 ሺሕ በላይ ናቸው፡፡

በትግራይ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ከተሰደዱት ውጭ፣ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸው ይነገራል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ ተቋማት 90 በመቶ የሚሆኑ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ አስታውቀው ነበር፡፡

መንግስት በበኩሉ ከአካባቢ ደህንነት ጋር በተያያዘ የተዘጉ ውስን መንገዶች ቢኖሩም በአካባቢው የሰብዓዊ ደጋፍ አገልግሎት እንዲስፋፋ እየሰራሁ ነው ብሎ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img