Thursday, October 10, 2024
spot_img

ኢዜማ በኦሮሚያ ክልል ስሬ ምርጫ ወረዳ ሊያደርግ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅት በአካባቢው አስተዳደር መከልከሉን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 30፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ክልል ስሬ ምርጫ ወረዳ ሊያደርግ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅት በአካባቢው አስተዳደር ክልከላ መስተጓጎሉን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው እንዳለው ዋና ጸሐፊው አቶ አበበ አካሉ የጎዳና ላይ የምርጫ ለማድረግ ወደ ስሬ ሄደው የነበረ ሲሆን፣ በስሬ ምርጫ ወረዳ ሻሜዳ ቀበሌ ሊቀመንበር እና የቀበሌው ሥራ አስኪያጅ የተመሩ ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል።

ከዚህ ቀደም ከምርጫው ሂደት ጋር በተያያዘ በሰጠው መግለጫ ከሌሎች ቦታዎች በተለየ ዕጩ ለማስመዝገብም ሆነ በነፃነት እንቅስቃሴ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ከተቸገረባቸው ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል አንዱ መሆኑን በመጥቀስ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቆ እንደነበር ያስታወሰው ፓርቲው፣ ከዚህ በተጨማሪም በየአካባቢው በሚገኙ የገዢው ፓርቲ አባላት ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዳይሆነ የሚፈፀሙትን እኩይ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ከአስር ቀናት በፊት በፊት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መጠየቁንም ገልጧል፡፡

ኢዜማ አሁን በኦሮሚያ ክልል በስሬ ወረዳ ምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ያጋጠመውን ችግር ለምርጫ ቦርድ የሚያመለክት መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img