Saturday, September 21, 2024
spot_img

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2014 በጀት ዓመት የ561 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አፀደቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ ለ2014 በጀት ዓመት የቀረበውን ረቂቅ በጀት አፅድቋል፡፡

በዚህም የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 561.7 ቢሊየን ብር እንዲሆን የቀረበው ረቂቅ በጀት፣ ምክር ቤቱ ከተወያየበት በኋላ ተቀብሎ ያጸድቅ ዘንድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል፡፡

ይህም ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንደሚያደርገው፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት ያጸደቀው የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 476 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img