Thursday, October 10, 2024
spot_img

የዓለም ባንክ በማሊ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ማቋረጡን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― የዓለም ባንክ በማሊ በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት ለሀገሪቱ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፎች ማቋረጡን አስታውቋል፡፡

የዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፉን ያቋረጠው በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ በአገሪቱ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡

የባንኩ የባማኮ ቢሮ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፤ መቀመጫውን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የዓለም ባንክ በማሊ እየተሰሩ ላሉ የልማት ስራዎች የሚያደርገውን ገንዘብ ድጋፍ በጊዜያዊነት አቋርጧል። በማሊ አሁንም ያለውን ሁኔታ ባንኩ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አክለው አስታውቀዋል።

የአፍሪካ ህብረትም ከዚህ በፊት በማሊ ላይ ጥሎት የነበረውን ከአባልነት የማገድ ውሳኔ፣ በማሊ በህዝብ ምርጫ የተመሰረተ መንግስት ስልጣን እስኪይዝ ድረስ ማራዘሙ ይታወሳል።

በተጨማሪም 15 አባል አገራት ያሉት የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በማሊ በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ምክንያት አስተላልፎት የነበረውን ከአባልነት የማገድ ውሳኔ በድጋሚ ማራዘሙ አይዘነጋም።

በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ በአገሪቱ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ተፈጽሟል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img