Thursday, November 21, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ1 ሺሕ 500 በላይ ፖለቲካዊ ግጭቶች ተከስተዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 28፣ 2013 ― በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ከመጋቢት 2010 አንስቶ ባለው ጊዜ 1 ሺሕ 557 የፖለቲካ ግጭቶች ተከስተው 7 ሺሕ 713 ሰዎች ሕይወታቸው መነጠቁን ኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ የተባለ ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል፡፡

እንደ ድረ ገጹ በነዚህ ፖለቲካዊ ግጭቶች ሰበብ 4 ሺሕ 203 በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ፖለቲካዊ ግጭቶች አሁንም መቀጠላቸውን ያመለከተው ድረ ገጹ፣ በተለይ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች መንግሥታትን መፈታተኑን ቀጥሏል ነው ያለው፡፡ ለአብነት ግንቦት 14፣ 2013 ጠዋት ላይ የጉሙዝ ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 17 ታጣቂዎች የቤንሻንጉል/ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰንን አቋርጠው ኦሮሚያ ክልል ነጆ ወረዳ በሚገኘው ያምበልጋራ ኦሊ ቀበሌ በግጭት ላይ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ሲል ገልጧል፡፡

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በመንግስት ኃይሎች እና በኦነግ ሸኔ መካከል የሚደረገው ውጊያ መቀጠሉን ያመለከተ ሲሆን፣ ግንቦት 14፣ 2013 የኦነግ ሸኔ አባላት ለስራ ወደ ቦሬ ቀበሌ የሚጏዙ የገላን ወረዳ ሰላም እና ደህንነት ሀይሎች ላይ አድፍጠው ጥቃት ማድረሳቸውንም ጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በአማራ ክልል የፖለቲካ አለመረጋጋት በሰሜን ጎንደር ዞን መመዝገቡንም የጠቆመው ኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ፣ ግንቦት 15 እና 17፣ 2013 ላይ የሱዳን ታጣቂዎች በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶቃ ቀበሌ የኢንቨስተሮች መኖሪያ ላይ ጥቃት እንዳደረሱ ነው ያመለከተው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img