Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የሚጠበቅበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ መንግሥት ገቢ አደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 27፣ 2013 ― በኢትዮጵያ በግል የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ዘርፍ ለመሳተፍ ጨረታውን ያሸነፈው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ባልቻ ሬባ እንዳሉት በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት 14 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኩባንያው ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ ለመንግሥት ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል። በዚህም መሰረት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አቶ ባልቻ ማናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ነዋይ የሚያፈስ ሲሆን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለጨረታው ማስኬጃ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት 500 ሚሊዮን ዶላር ብድር አግኝቷል። በሌላ በኩል ዳይሬክተሩ ሁለተኛውን የቴሌኮም ኦፕሬተር ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ በጨረታው ላይ አዳዲስ የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡና የመሰረተ ልማት ዝርጋታው ላይ መሳተፍ የሚችሉበት ዕድልም ሊታይ ይችላል ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img