Sunday, November 24, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በሌጎስ ካረፈ በኋላ ከመንገድ ወጥቶ እንደነበር ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 27፣ 2013 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የበረራ ቁጥር ኢቲ 3905 አውሮፕላን ናይጄሪያ ሌጎስ ደርሶ ካረፈ በኋላ ወደ መቆሚያ ስፍራው እየሄደ ሳለ ከመንገዱ ወጥቶ እንደነበር ፍላይት ግሎባል በድ ረገጹ አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳረጋገጠው ወደ ካርጎ የተቀየረው የመንገደኞች ቦይንግ 777-300 ግዙፍ አውሮፕላን ካጋጠመው ክስተት በኋላ ወደ ሥራ ተመልሷል።

አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያዋ ሌጎስ ጭነት ይዞ ከበረረ በኋላ በሌጎስ አየረ ማረፊያ አርፎ ወደ መቆሚያው እየሄደ ሳለ የአውሮፕላኑ በስተግራ በኩል ያለው ጎማ ከአስፓልቱ መውጣቱን አየር መንገዱ አስታውቋል።

በፍላይት ግሎባል ድረ ገጽ ላይ የተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል የአውሮፕላኑ በስተግራ በኩል ያለው ጎማ ጭቃ ውስጥ ገብቶ መግባቱ ያሳያል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ክስተቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አውሮፕላኑ ምንም አይነት ጉዳት ሳያጋጥመው በመብረር ወደ አዲስ አበባ መመለሱን አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ከአስፓልቱ እንዲወጣ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ በአየር መንገዱ መግለጫ ላይ አልተገለጸም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img