Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ኤርትራ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ መሬት በከፊል እያስወጣች ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 26፣ 2013 ― ከጥቅምት የመጨረሻ ሳምንት አንስቶ በፌደራል መንግሥት እና በሕወሃት ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የዘለቁት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት መጀመራቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ መሬት ላይ ከሚገኙት መካከል በትላንትናው እለት ሁለት የኤርትራ ክፍለ ጦሮች ከማእከላዊ ትግራይ ኃይላቸውን ሲያስወጡ እንደነበር ነው የተነገረው፡፡ እነዚህ ከክልሉ እየወጡ እንደሆኑ የተነገረላቸው የ16ኛ እና የ57ኛ ክፍለ ጦሮች ሲሆኑ፣ ቀድሞ ወደ አድዋ በማቅናት ኋላም ወደ አገራቸው አምርተዋል ነው የተባለው፡፡

ያለፉትን ስድስት ወራት በትግራይ ክልል የቆየው የኤርትራ ወታደሮች በክልሉ በንጹሐን ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸማቸውን፣ ሴቶችን አስገድደው ሲደፍሩ እንደነበርና ሌሎች አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽሙ መቆየታቸውንም የተለያዩ አካላት ሲገልጹ ሰንብተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img