Thursday, October 10, 2024
spot_img

በሶማሌ ክልል በግመል እንስሳት ላይ ምንነቱ ያልታወቀ አዲስ ወረርሽኝ መታየቱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 26፣ 2013 ― ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ በግመል ላይ የታየው ምንነቱ በደንብ ያልታወቀ ወረርሽኝ መከሰቱን የሶማሌ ክልል የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አሕመድ ኑር ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው እንዳሉት ወረርሽኙ ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑ እና አለመሆኑን ስላልታወቀ ኅብረተሰቡ የግመል ሥጋ እና ወተት ሲጠቀም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ተመሳሳይ ምልክት ያለው የእንስሳት በሽታ በኬንያና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎችም መታየቱን ቢሮ ጠቁሟል።

የዚህ አዲስ ያልታወቀው በሽታ ናሙና ተወስዶ በፌዴራል ደረጃ በላብራቶሪ እየተመረመረ መሆኑንና በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንደሚሰጥ የሶማሌ ክልል የአርብቶ አደርና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አሕመድ ኑር ማስታወቃቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም የክልሉ ኮምዮኒኬሽን ቢሮ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img