Thursday, October 10, 2024
spot_img

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የኤርትራ ወታደሮች ‹‹አንድ ቀን›› እንደሚወጡ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 26፣ 2013 ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያ መሬት ላይ የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮች ‹‹አንድ ቀን ይወጣሉ›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የመንግሥት አቋም ይወጣል የሚል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና፣ ለቀው እንደሚወጡም ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

በጥቅምት የመጨረሻ ሳምንታት የተቀሰቀሰውን የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሃት ኃይሎችን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የዘለቁት የጎረቤት አገር ኤርትራ ወታደሮች፣ ካሉበት የትግራይ ክልል እንደሚወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ተስማምተናል ካሉ ከስምንት ሳምንታት በላይ የተቆጠረ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ የመውጣት ምልክት እንዳላሳዩ ይነገራል፡፡

ወታደሮቹ የኢትዮጵያን መሬት ለቀው እንዲወጡ በተለይ አሜሪካ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ስታወጣ የሰነበተች ሲሆን፣ በቅርቡም በሁለቱም አገራት ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ማዕቀብ መጣሏ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img