Tuesday, October 8, 2024
spot_img

ትዊተር ባለ ከፍያ አገልግሎት ጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― በዓለማችን ከ330 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ትዊተር የተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ፣ ወርሃዊ 3 ዶላር የሚያስከፍልበትን አዲስ አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

‹ትዊተር ብሉ› በተባለው በዚሁ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ትዊት ካደረጉ ወይም ከላኩ በኋላ ውሳኔያቸውን መቀልበስ የሚያስችል አሠራር አለው ተብሎለታል፡፡

በትዊተር ብሉ ተጠቃሚዎች ትዊት ያደረጉትን ጽሑፍ አልያም ፎቶ በአንድ አቃፊ (ወይም ፎልደር) ማስቀመጥ እንደሚችሉም ኩባንያው አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ይህ አገልግሎት ለአይፎን ተጠቃሚዎች የቀረበ መሆኑን ነው የተነገረው፡፡

ትዊተር ኩባንያ በፈረንጆቹ 2020 የተጣራ ዓመታዊ ትርፉ 1 ነጥብ 13 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img