Sunday, September 22, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የገጠማትን ጉዳይ ለመፍታት በወዳጆች በኩል እየተሠራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ጋዜያዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የገባችበትን አለመግባባት ለመፍታት በወዳጆች በኩል እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ደረጃ ‹‹ጉዳዩን የማጋጋል ፍላጎት የለንም›› ያሉት ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና፣ ‹‹የተፈጠረው ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ በጋራ ወዳጆቻችን በኩል እየተነጋገርን ነው ያለነው›› ሲሉ መናገራቸውን የአል ዓይን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ቃል አቀባዩ ከሰሞኑ ኢትዮጵያ የተገኙት የአሜሪካው ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ጉብኝትም የዚሁ አካል ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው፣ ‹‹የአሜሪካ አቋም ይቀየራል ብለን ነው የምናምነው፣ መቼና እንዴት የሚለው ግን እነሱን የሚመለከት ነው›› ብለዋል፡፡

አምባሳደር ዲና፣ ሴናተሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መገናኘታቸውን እና ‹‹ውጤታማ ጉብኝት›› ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ‹‹ለኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ አጋርነታቸውን ያንፀባረቁ ወዳጅ ናቸው›› ሲሉም አምባሳደር ዲና ሴናተሩን አወድሰዋል፡፡ አክለውም ‹‹የሃገራቱን ግንኙነት ለመታደግ የመንግስትን ጥረት ከነጉድለቱም መደገፍና መነጋገር እንጂ ሌላ ጫና አያስፈለግም የሚሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ናቸው›› ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪከ ልዩ መልዕክተኛው ጄፍሪ ፌልትማንም ወደ ኢትዮጵያ ዳግም እንደሚመጡ ገልጸው፣ ነገር ግን የሚመጡበት ቀን እንዳልተቆረጠ ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img