Sunday, September 22, 2024
spot_img

ከትግራይ ክልል አጠቃላይ ነዋሪ ከ90 በመቶ በላይ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገው የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከአጠቃላዩ ነዋሪ ከ90 በመቶ በላይ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታውቋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ባወጣው መግለጫው በክልሉ አስፈላጊ ላለው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ 203 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል እንደሚያስፈልግ ነው የጠቀሰው፡፡

በትግራይ ክልል ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ምክንያት 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ እንደሚያፈልገውም የዓለም የምግብ መርኃ ግብር ቃል አቃባይ ቶምሶን ፒሪ ከጄኔቫ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ቃል አቃባዩ «በክልሉ ረሃብ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሸጋገር ያሳስበናል» ብለዋል።

የዓለም የምግብ መርኃ ግብር በሰሜን ምዕራብ እና በደቡባዊ የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመጋቢት ወር ከአንድ ሚሊዮን ለሚልቁ የምግብ ርዳታ ፈላጊዎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። በክልሉ እስከሚቀጥሉት ስድስት ወራት መጨረሻ በረሃብ ምክንያት የሰዎች ሕይወት እንዳይጠፋ እና የተጀመረውን የምግብ ድጋፍ አጠናክሮ ለማዳረስ የተጠየቀው ገንዘብ በአስቸኳይ ሊቀርብ እንደሚገባ ድርጅቱ አሳስቧል።

መንግስት በበኩሉ በትግራይ ክልል በሁለተኛ ዙር አቅርቦቱ ለ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ነዋሪዎች ርዳታ ማድረጉን ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ያሳወቀ ሲሆን፣ የርዳታ አቅርቦቱን ለማዳረስም ጥረት እያደረገ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img