Sunday, November 24, 2024
spot_img

የአሜሪካው ልዩ መልእክተኛ በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የሳዑዲ እና ኤሜሬትን ጨምሮ የአራት አገራት መሪዎችን ሊያነጋግሩ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― የአሜሪካው የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ጅፍሪ ፌልትማን በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ወደ ኳታር፣ ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት እና ኬንያ አቅንተው መሪዎቻቸውን እንደሚያነጋግሩ የአገሪቱ የውች ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ፌልትማን ከነዚህ አራት አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በአጠቃይ የተረጋጋች ምሥራቅ አፍሪካን ለመፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ነው የተባለው፡፡

የአሜሪካው የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከዚህ ከሳምንታት በፊት በተመሳሳይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ግብጽን ጎብኝተው ከመሪዎቹ ጋር መምከራቸው አይዘገነጋም፡፡

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ከባለሥልጣናቱ መልካም ፊት እንዳላገኙ የተነገረ ሲሆን፣ ወደ አገራቸው ከተመለሱ ከቀናት በኋላ አሜሪካ በሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እና የኢኮኖሚ ማበረታቻ ማእቀብ መጣሏም የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img