Sunday, October 6, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለፀጥታ ስጋት ናቸው ያላቸውን 999 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 24፣ 2013 ― ኮሚሽኑ በከተማዋ በልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት ናቸው ያላቸውን ወደ 999 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ በምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች ኮሚሽኑ በሰባት ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22፣ 2013 ባከናወነው ኦፕሬሽን ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮች እና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ ናቸው ብሏል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አብዛኞቹ ማስቲሽና ቤንዚን በመጠቀም እራሳቸውን በማደንዘዝ የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን ሲያውኩ እንደነበር በተለይ የትራፊክ መብራት ካስቆመው ተሽከርካሪ ላይ ስፖኪዮ ገንጥለው እንደሚወስዱ፣ ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ ሞባይል ስልክ፣ የአንገት ሃብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በጠራራ ፀሀይ ቀምተው እንደሚሰወሩ ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡

በተጨማሪም ሴት አሽከርካሪዎች አደጋ ሳያደረሱባቸው አደጋ እንዳደረሱባቸው በማስመሰልና በማዋከብ ገንዘብ እንደሚቀበሉ፣ የትራፊክ አደጋ ሲያጋጥም ልዩ ልዩ ስልቶችን በመጠቀም ንብረቶችን እንደሚስርቁ በጥቅሉ ትኩረታቸውን በዋና ዋና አደባባይ የትራፊክ መብራት በያዘው ተሽከርካሪ ላይ አድርገው ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር ኮሚሽኑ ከህዝብ ከደረሰው ጥቆማና ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን ኮሚሽኑ ገልጧል፡፡

ግለሰቦቹ በምሽት የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር በመረጋጋጡ በተለይ የውጪ ሀገር ዜጎችንና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን በማዋከብና በማስጨነቅ በከተማችን መልካም ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲፈጥሩ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የተሰወኑት ግለሰቦች የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በከተማው የሚስተዋሉ መሰል ስጋቶችን ለመቀነስ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ህግን የማስከበር ተግባርና በተጠርጣሪዎቹ ላይ እየተደረገ ያለው ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ በወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ግለሰቦች መካከል እንደ ድርጊታቸው መጠንና ስፋት በህግ የሚጠየቁት እንተጠበቀ ሆኖ እድሜያቸው አንስተኛና በወንጀል ድርጊት ተሳትፏቸው እጅግ ቀላል የሆኑት ደግሞ ከሚመለከታው የአስተዳደር አካል ጋር በመቀናጀት የተሃድሶ ስልጠና እንደሚሰጣቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img