Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የአሜሪካ ኤምባሲ እገዳ ከተጣለባቸው አካላው ውጪ አገልግሎት እየሰጠሁ እገኛለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 24፣ 2013 ― በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አገሪቱ የጉዞ እቀባ ከጣለችባቸው የፌዴራል መንግስት ባለስልጣት፣ የአማራ ልዩ ኃይልንና የህወሃት አባላት ውጪ ለትምህርት፣ ለስራና ለሌሎችም ጉዳዮች ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ዜጎችን እያስተናገድኩ እንደምገኝ እወቁት ብሏል፡፡

አገሪቱ ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ክልከላ፣ የአሁንና የቀድሞ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ባለስልጣትን የሚቨም ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ የፀጥታ አካላትን እንደሚያካትት ታውቋል።

ኤምባሲው በትግራይ ክልል ያለው አለመረጋጋት እንደሚያሳስበው የገለፀ ሲሆን፣ ችግሩ ተባብሶ ረሃብን ያስከትላል የሚል ስጋት እንዳለውም ነው ያስታወቀው፡፡

አሜሪካ ከቀናት በፊት የጣለችው የቪዛ እቀባ የተቃውሞ እና የድጋፍ ምላሾችን አስተናግዷል፡፡ ባእቀቡን ከተቃወሙት መካከል የሆኑት የአሜሪካው ሴናተር ጂም ኢንሆፍም በትላንትናው እለት ኢትዮጵያ መምጣታቸው መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡

እኚሁ ሴናተር በዛሬው እለት ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አፈ ጉባኤ ታገሠ እና ሴናተር ጀምስ ኢንሆፎ በወቅታዊ ቀጠናዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img