Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በትግራይ ግጭት አሁንም በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች የመቀነስ አዝማሚያ እንዳላሳዩ የዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 24፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰ 7 ወራት ገደማ እየተጠጋ ቢመጣም፣ አሁንም ቢሆን በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች የመቀነስ አዝማሚያ እንዳላሳዩ የዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

እስካሁን ድረስ ከ6 ሺሕ በላይ ከቤተሰቦቻቸው የተለዩ ሕፃናት ለደኅንነት ጥበቃ እና ለእርዳታ መመዝገባቸውን የገለጸው ድርጅቱ፣ በጸጥታ ችግር እና በግጭቱ ተሳታፊ በሆኑ አካላት በተጣሉ የመዳረሻ ገደቦች ምክንያት ድርጅቱ ሊደርስባቸው ባልቻለባቸው አካባቢዎች ድጋፍ የሚፈልጉ ብዙ ልጆች ሊኖሩ እንደሚችሉም ስጋቱን ገልጧል፡፡

በተጨማሪም የልጆችን ቤተሰብ ማፈላለግ እንዲሁም የቴሌኮሙኒኬሽን ውስንነት እና የማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኞች ማነስ ለሥራው እንቅፋት እንደሆኑበትም በመግለጫው አንስቷል፡፡

የሕፃናት መርጃ ድርጅቱ አሁንም ድረስ ሴቶችና ልጃገረዶች ለአስደንጋጭ የፆታ ጥቃቶች እየተዳረጉ ነው ያለ ሲሆን፣ በትግራይ ግጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 540 የሚደርሱ በሕይወት የተረፉ የጥቃት ሰለባዎች እርዳታ እንደተደረገላቸው ስለመሆኑም አመልክቷል፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት ሪፖርት በትግራይ ክልል ባለው ግጭት በትንሹ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ከ720 ሺሕ የሚልቅ ቁጥር ያላቸው ሕፃናት ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img