Sunday, September 22, 2024
spot_img

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ በ19 የህወሓት አመራርና አባላት ላይ እገዳ ተጣለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 24፣ 2013 ― ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ በ19 የህወሓት አመራርና አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ ቋሚ ንብረቶቻቸው ላይ እገዳ መጣሉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል።

ግብረ ሃይሉ እንዳስታወቀው በአሸባሪው የሸኔ ቡድን ሲደግፉ የነበሩ 141 ተጠርጣሪ ግለሰቦች የፋይናስ ስርአት እንዲቀርጥና ገንዘባቸው እንዲታገድ ተደርጓል፡፡

የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይሉ በአሁኑ ወቅት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው የህወሓት ቡድን ጋር ተሰልፈው ሀገር ለማተራመስና ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች፤ ቀደም ሲል ለህዝብና ለሀገር ጥቅም እንዲሰሩ የተጣለባቸውን ከባድ ሀላፊነት ወደ ጎን በመተው ከፍተኛ ሃብት በመመዝበር በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ንብረቶች አፍርተዋል።

በተጨማሪም በፈፀሙት የሀገር ክህደት ወንጀል የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸው እንደነበርም አስታውሷል።

መግለጫው አክሎም፤ እነዚህ ግለሰቦች በአንድ በኩል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶችን በመፈጸም፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሰው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጋር በአመራርነትና በአባልነት እየተሳተፉ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከህዝብና ከሀገር በመዘበሩት ሃብት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የገነቧቸውን የመኖሪያ ህንፃዎችና ያቋቋሟቸውን የንግድ ድርጅቶች በቤተሶቦቻቸውና በወኪሎቻቻው አማካኝነት በማከራየት በወር እስከ 9ሺህ ዶላር ድረስ ይሰበስቡ ነበር።

ግለሰቦቹ ይህን ከኪራይ የሚገኝ ከፍተኛ ገቢ በህገወጥ መንገድ በመላክ የሽብር ቡድኑን ህልውና ለማስቀጠል ለተለያዩ የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች ግዢ እንዲሁም ለሎጀስቲክስ አቅርቦት ከማዋል ባሻገር ንብረቶችን በመሸጥም ጭምር ሃብት የማሸሽ ስራ ለመስራት እየተንቀሳቀሱ እያሉ በተደረገባቸው ጥብቅ የመረጃ ስራና ክትትል ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ለሚመለከተው የመንግስት አካል በማቅረብ እግዱ በፍርድ ቤት በኩል እንዲፈጸም መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ንብረታቸውን እንዳያንቀሳቅሱና እንዲታገድ የተደረገባቸው የሸብርተኛው የህወሓት ቡድን አመራርና አባላት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በቅፅል ስሙ ወዲ ወረደ፣ ሌተናል ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑ በቅፅል ስሙ ፍስሃ ማንጁስ፣ ሜጀር ጀነራል አበበ ተ/ሀይማኖት በቅፅል ስሙ ጆቤ፣ ሜጀር ጀነራል ሀልፎም እጅጉ በቅፅል ስሙ ወዲ እጅጉ፣ ሜጀር ጀነራል ተስፋዬ ግደይ፣ ብርጋዴር ጀነራል ሃ/ስላሴ ግርማይ በቅፅል ስሙ ወዲ እንቤተይ፣ ብርጋዴር ጀነራል ምግበ ሀይለ፣ ብርጋዴር ጀነራል ተክላይ አሸብር በቅፅል ስሙ ወዲ አሸብር፣ አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፤ አቶ ሀሰን ሽፋ በድምሩ አስራ ዘጠኝ መሆናቸውን የጋራ ግብረኃይሉ ገልጿል።

መግለጫው አክሎም መቀሌ ከተማ ሆነው ለሽብር ቡድኑ መረጃ ሲሰጡ፤ የፋይናንስና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን በድብቅ ሲያቀርቡ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብሶችን በመልበስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ ተመሳስለው ጥቃት ሲፈጽሙ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል 14 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሷል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ፤ለሰብአዊ ድጋፍ በመጓጓዝ ላይ የነበሩና እያንዳንዳቸው 20 ሌትር የምግብ ዘይት የያዙ 2200 ጄሪካኖችን የጫነ አንድ ተሽከርካሪ ከእነ ተሳቢው አስገድደው አቅጣጫውን እንዲቀይር በማድረግ፤ በድብቅ ለሽብር ቡድኑ ለመላክ ሲሞክሩ መሆኑን አትቷል።

በተመሳሳይም ሀገር በማፍረስ ሴራ ውስጥ በመሳተፍ ያለውን የአሸባሪውን የሸኔ ቡድንን እንቅስቃሴ በገንዘብ ሲደግፉ የነበሩ የ141 ተጠርጣሪ ግለሰቦች የፋይናንስ ስርዓት እንዲቋረጥና በአካውንታቸው ውስጥ የተገኘ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲታገደ መደረጉንም የጋራ ግብረ ኃይሉ አመልክቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img