Friday, November 22, 2024
spot_img

ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ የፌዴራል መንግሥቱን የትግራይን ጦርነት በመጀመር ከሰሱ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 23፣ 2013 ― በአሁኑ ወቅት በረሃ ወርዶ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተፋለመ ነው የሚባለው ሕወሃትን የወታደራዊ ክንፉን እየመሩ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ የፌዴራል መንግሥቱን የትግራይን ጦርነት በመጀመር ከሰዋል፡፡

ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ ይህንኑ ካልታወቀ ቦታ በድምጺ ወያኔ የፌስቡክ ገጽ በተላለለፈ ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ ጦርነቱን አስመልክቶ እኛም ተፈጥሯችንን ሳንቀይር፤ እነሱም ተፈጥሯቸውን ሳይቀይሩ ጦርነቱ ሊቀር አይችልም ነበር ሲሉ የተደመጡት ሌተናል ጀነራሉ፣ አሁንም ጦርነቱ መውጫው ቀላል አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡

በ1993 የሕወሃትን ክፍፍል ተከትሎ ከጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹምነት ተነስተው በግል ንግድ ተሰማርተው እንደነበር የሚነገርላቸው ሌተናል ጀነራል ጻድቃን፣ አሁን በትግራይ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ እንዲበጅ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሕዝብ መርጦታል ያሉትን ሕወሃትን ወደ መንግሥት ሥልጣን ይመለስ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል በፌዴራል መንግሥቱ የተመሠረተውን የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደርን አስመልክቶም ያነሱ ሲሆን፣ የክልሉ አስተዳደር የሬድዮና ቴሌቪዥን ጩኸት አሰምቶ በአንድ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ የደረሰብትን እንዲረሳ ይፈልጋል ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረውበታል፡፡

ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ጦር መርተው ወደ ከተማው ዘልቀዋል የሚባልላቸው ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ፣ የኢፌዴሪ መንግሥት የመጀመሪያው ኢታማጆር ሹም ሆነው ለ7 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img