Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በቦረና ዞን 300 ሰዎች በመንግሥት ግድያ ይፈፀምብናል በሚል ስጋት ወደ ኬንያ ሸሽተዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 21፣ 2013 ― በደቡብ ኦሮሚያ ቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ጎቱ ቀበሌ 300 ሰዎች በመንግሥት ግድያ ይፈፀምብናል በሚል ስጋት ወደ ኬንያ መሸሻቸውን አምባ ዲጂታል ከአካባቢው ምንጮች ሰምቷል።

ለነዋሪዎቹ ሽሽት ሰበብ ነው የተባለው ባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 አንድ የአካባቢው ወጣት የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ነህ በሚል በቤተሰቦቹ ፊት በመንግሥት ታጣቂዎች መገደሉን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎቹ ሌሎች እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጓቸው 17 ሰዎች አሉ የሚል መረጃ መሠራጨቱ ነው።

እንደ ምንጮች ከሆነ በእለቱ የኦነግ ሸኔ አባል ነው የተባለውን ወጣት ተኩሶ የገደለው የሚዮ ወረዳ አስተዳደር አቶ ጃርሶ አና ነው።

አስተዳዳሪው ግድያውን ከፈጸመ በኋላ የሟች ቤተሰቦች አስከሬን እንዳያነሱ መከልከላቸው ተነግሯል።

ግድያው በተፈጸመበት የኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ከሸሹት በተጨማሪ ነዋሪዎች የኦነግ ሸኔ አባል ናችሁ በሚል ምክንያት ለእስር እየተጋለጡ መሆኑንም ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።

ፎቶ፡ ወጣቱን ገድሏል የተባለው ጃርሶ አና እና የሟች እናት

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img