Saturday, November 23, 2024
spot_img

ከሽረ ከተማ ስደተኞች ማዕከል ታፍነው የተወሰዱ ስደተኞች መመለሳቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 21፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ሽሬ እንዳሥላሴ ከተማ ከተፈናቃዮች ማቆያዎች በወታደር ታፍነው ተወሰዱ የተባሉ ሰዎች መመለሳቸው ተነግሯል፡፡

ስደተኞቹ በኢትዮጵያና በኤርትራ ወታደሮች ታፍነው መወሰዳቸውን እንዲሁም ድብደባም ተፈጽሞብናል ማለታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል፡፡

ከሰኞ ግንቦት 16፣ 2013 ምሽት ጀምሮ በትግራይ ክልል፤ ሽረ ከተማ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው የመጠለያ ካምፖች ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱ በርካታ ተፈናቃዮች ለሦስት ቀናት ከታፈኑ በኋላ መለቀቃቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ስደተኞቹ ከፅሀየና ዓዲንፊቶ ከተባሉ ት/ቤቶች እንዲሁም የተፈናቃዮች ማእከላት በወታደሮች ከተወሰዱ በኋላ ከከተማዋ ወጣ ብሎ ወደ ዓዲ ዳዕሮ የሚባል ከተማ በሚወስድ መንገድ ጉና በተባለ አዳራሽ እንደቆዩ ነው የገለጹት፡፡

ከስደተኞች መካከል የሆኑ እንደሚሉት ከሆነ ደረታቸውንና ጀርባቸው በዱላ በደረሰባቸው ድብደባ ተጎድተዉ አሁን ተኝተዉ እንዳሉ የገለጹ ሲሆን፣ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ማእከሉ እንዲገቡ ባይፈቀድም ወታደሮቹ ግን ይህን ህግ ጥሰው በጨለማ ገብተው አፍኖ ወስዶናል ብለዋል፡፡

ጨምረውም ማታ ሶስት ሰአት አካባቢ ወደ አጠለልንበት ቦታ መጥተዉ በበትር እየደበደቡ ከመጠለያው ካስወጧቨው በኃላ በግራና በቀኝ እንዲሁም ከኋላ በስናይፐር አጅበው ጉና ወደ ተባለው አዳራሽ ወስደውናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዱላ ጆሯቸው ላይ ተመተዉ እየታከሙ እንደሆኑ የገለጹት ሌላኛው ስደተኛ በበኩላቸው፣ ሦስት ቀን ታፍነው ከተለቀቁ ብኃላ በተፈናቃዮች ማዕከላት የነበሩት ስደተኞች በስጋት ወደ ነዋሪው ሕዝብና ወደ ገጠር ሸሽቶ ነው የጠበቁን ብለዋል፡፡

ጉዳዩን በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሙሽን በሽረ ከተማ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው የመጠልያ ካምፖች ውስጥ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱ በርካታ ተፈናቃዮች ስላሉበት ሁኔታ ክትትል በማድረግ ላይ ነኝ ሲል ከትላንት በስትያ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img