አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ግንቦት 21፣ 2013 ― ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጉዞ ማዕቀብ እና የኢኮኖሚ ማበረታቻ ማዕቀብ የጣለው የባይደን አስተዳደር የልማት ባንኮች ለኢትዮጵያ ብድር ከመስጠት እንዲታቀቡ መጠየቁን የዘገበው ብሉምበርግ ነው፡፡
ይህንኑ የአሜሪካ አቋም የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሮበርት ጎዴክ በአሜሪካ ሴኔት አንጸባርቀዋል፡፡
እንደ ጎዴክ ከሆነ አሁንም በትግራይ ክልል በምግብ እጥረት የሚሞቱ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ወጥተዋል፡፡
በተመሳሳይ የአሜሪካ ሴኔት በተሰበሰበበት ከትላንት በስትያ ሐሙስ ጂም ሪሽ የተባሉ ሴናተር ሀገራቸው በሰብዓዊ መብት ጥሰት የምትከሳቸውን ማዕቀብ በመጣል ለመቅጣት የምትጠቀምብትን “የማግኒትስኪ ድንጋጌ” በኢትዮጵያ ላይ እንድትጠቀም ጥቆማ ሰጥተዋል።