Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ምርጫውን አቋርጦ ሊወጣ እንደሚችል አስጠነቀቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ገዢው ፓርቲ እያደረሰብኝ ነው ባለው ጫና ምክንያት መጪውን ምርጫ አቋርጦ ሊወጣ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ዎሕዴግ በአባላቱ እና ደጋፊዎቹ ላይ ተፈጽመዋል ያላቸው የምርጫ ስነ ምግባር ጥሰቶች እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በገለልተኛ አካል አጣርቶ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

ዎሕዴግ ማስጠንቀቂያ ያዘለውን መግለጫ ለማውጣት የተገደደው፤ በፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው “እስራት እና አፈና ከአቅሙ በላይ እየሆነ በመምጣቱ ነው” ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ጎበዜ ጎአ ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ቀግቧል።

“የምርጫ ቅስቀሳ ከጀመርን ወዲህ የብልጽግና ጡንቻዎች ሲያርፉብን ቆይተዋል” ሲሉ የተናገሩት አቶ ጎበዜ፤ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለበርካታ ጊዜ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካ መቅረቱን አስረድተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img