Sunday, November 24, 2024
spot_img

የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በትግራይ የሚፈጽሙት ሰቆቃ መበርታቱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― በትግራይ ክልል የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በዜጎች ላይ የሚፈጽሙት ሰቆቃ መበርታቱን አሶሽየትድ ፕረስ ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

የዜና ተቋሙ በክልሉ ሪፖርተሮቹ በተዘዋወሩባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በርከት ብለው እንደሚታዩ ያመለከተ ሲሆን፣ በክልሉ በተለይ ሴቶች ላይ የሚፈጽሙት አስገድዶ መድፈር፣ ግድያዎች እና የንብረት ዘረፋ መገለጫቸው መሆኑንም አስፍሯል፡፡

አሶሽየትድ ፕረስ በክልሉ ያገኘኋቸው ሁሉም ሰዎች በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች ለቀው ሳይወጡ በክልሉ ሰላም ይመጣል የሚል ተስፋ እንደሌላቸው ነግረውኛል ነው ያለው፡፡

በጥቅምት የመጨረሻ ቀናት የተቀሰቀውን የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሃትን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የዘለቁ የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአገሪቱ ባለሥልጣት ጋር ለቀው እንዲወጡ ተስማምተናል ካሉ በርካታ ሳምንታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ እስካሁንም ድረስ ይህ እየተፈጸመ ስለመሆኑ ጠቋሚ መረጃ አልወጣም፡፡

ይህንኑ በተመለከተ ሪፖርት ያወጣው ጀኖሳይድ ወች የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ወታደሮቹ የኢትዮጵያን መሬት የመልቀቅ ምልክት እንዳላሳዩ በሪፖርቱ አረጋግጧል፡፡

ጄኖሳይድ ወች ወታደሮቹ አሁንም ቀድሞ ከፈጸሙት የባሰ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይፈጽሙ በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በትላንትናው እለት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img