አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― የሩሲያው ፕሬሬዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው እለት ለሚከበረው የግንቦት 20 በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን ለፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ልከዋል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የላኩትን የእንኳን አደረሳችሁ ደብዳቤ በአዲስ አበባ የሩሲያ ኢምባሲ በትዊር ገጹ ላይ አስነብቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በደብዳቤያቸው የኢትዮጵያና የሩስያ ግንኙነት የቆየና የጠበቀ ነው ያሉ ሲሆን፣ የሁለቱ ሃገራት የጠነከረ ትብብር በሁለም ቦታ ላይ የሁለቱ ሕዝቦች ፍላጎት እንዳሟላ እርግጠኛ ነኝ፣ ይህም የቀጠናውን ደኅንነት እና መርጋጋት ያጠናክራል ብለዋል፡፡
በያመቱ ደርግ ከሥልጣን የወረደበትን እለት አስመልክቶ በደማቅ ሁኔታ ይከበር የነበረው የግንቦት 20 በዓል፣ ባለፉት ዓመታት የሕወሃትን ከማእከላዊ መንግሥት ሥልጣን መወገድ ተከትሎ መደበኛ ተቋማት ሥራ ከመዝጋቸው ውጭ ሲከበር አይስተዋልም፡፡