Sunday, October 6, 2024
spot_img

አሜሪካ ተጨማሪ ማእቀብ ልትጥል እንደምችል የአገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ግንቦት 20፣ 2013 ― ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የጣለው የባይደን አስተዳደር ተጨማሪ ማእቀብ ሊጥል እንደሚችል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊው ሮበርት ጎዴክ ነግረውኛል ብሎ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል በንጹሐን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እጅጉን ዘግናኝ መሆኑን ያመለከቱት ሮበርት ጎዴክ፣ ተፈጽሟል ያሉትን የሴቶች መደፈር፣ የንጹሐን ግድያ እና የንብረት ውድመት ኮንነዋል፡፡ አክለውም አሜሪካ አሁንም በክልሉ ተፋላሚ ኃይሎች ግጭቱን እንዲያቆሙ፣ የሰብአዊ አቅርቦት እንዲደርስ እንዲያደርጉና የሚፈጸሙ ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲከላከሉ መጠየቋን ያስታወሱት ሮበርት ጎዴክ፣ ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉ የባይደን አስተዳደር ተጨማሪ ማዕቀብ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በትግራይ ተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በጉዳዩ ላይ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ስታወጣ የሰነበተችው አሜሪካ፣ ከጥቂት ቀናት በፊት ለምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ አድርጋ የሾመቻቸው አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ልካ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለሥልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

ሆኖም መልእክተኛዋ ከመሪዎቹ በጎ ምላሽ አላገኙም መባሉን ተከትሎ፣ በሁለቱም አገራት ባለሥልጣናት ላይ የጉዞና የኢኮኖሚ ማበረታቻ መእቀብ መጣሏ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img